ዩክሬን ውስጥ በተጎዱ ወታደሮች እና ሲቪሎች ላይ አደገኛ የህክምና ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን የሩሲያ ባለስልጣን ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ዩክሬን ውስጥ በተጎዱ ወታደሮች እና ሲቪሎች ላይ አደገኛ የህክምና ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን የሩሲያ ባለስልጣን ተናገሩ በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኪዬቭ አገዛዝ ወንጀሎች ልዩ መልዕክተኛ ሮድዮን ሚሮሽኒክ ለስፑትኒክ እንደተናገሩት፤ ሀገሪቱ በሌላ ቦታ የማይፈቀዱ ምርመራዎች መሞከሪያ ቦታ ሆናለች። ሚሮሽኒክ እንዳብራሩት፤ በዩክሬን የጦር ግንባር የሕክምና ባለሙያዎች ያለምንም ፈቃድ መድሐኒት ወይም ክትባት ሊጠቀሙ ይችላሉ። የመድሐኒቱን ውጤታማነት ጉዳት በደረሰባቸውን ሰዎች ላይ ሊሞክሩ ይችላሉ ሲሉም አክለዋል። ከቆሰሉ የዩክሬን ወታደሮች ወይም ሲቪሎች የተመረጡ "መሞከሪያዎች" መጨረሻቸው የቀዶ ጥገና ጠረጴዛ እንደሆነ ልዩ መልዕክተኛው ተናግረዋል። እንደ ሚሮሽኒክ ገለፃ፤ ምርመራዎቹ የሚካሄዱት የተለያዩ መድሐኒቶች በመሞከሪያዎቹ ላይ የሚፈጥሩትን ምላሽ በመረጃ መልክ ለመሰብሰብ ነው ብለዋል። ምስሉ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የመነጨ ነውበእንግሊዘኛ አንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0