በአንጎላ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ከአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ በትንሹ 108 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
በአንጎላ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ከአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ በትንሹ 108 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ ከጥር 7  ጀምሮ በአንጎላ 3፣147 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው እንደተረጋገጠ እና ግማሽ ያህሉ በመዲናዋ ሉዋንዳ መመዝገባቸውን የጤና ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በበሽታው የተያዙት እድሜያቸው ከሁለት እስከ 100 የሚደርሱ ሲሆን፤ በሉዋንዳ ቢያንስ 48 እንዲሁም በጎረቤት ቤንጎ ግዛት 43 ሰዎች ሞተዋል። ኮሌራ በቫይሪዮ ኮሌሬ ባክቴሪያ የተበከለ ምግብ ወይም የመጠጥ ውሃ በመመገብ የሚከሰት ከባድ እና ገዳይ የሆነ የአንጀት ኢንፌክሽን ነው። ኢንፌክሽኑ ከባድ ተቅማጥ፣ ተውከት እና የጡንቻ መሸምቀቅ ያስከትላል። ሆኖም ከባድ የሆነውን ህመም በአፍ በሚወሰድ ፈሳሽ እና አንቲባዮቲኮች ውጤታማ በሆነ መንገድ ማከም ይቻላል። እንደ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ፤ የኮሌራ ሞት በ2023 ቀድሞ ከነበረው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ71% ከፍ ብሏል። በሽታው በመካከለኛው ምስራቅ እና እስያ በ32% ሲቀንስ በአፍሪካ ግን በ125% ጨምሯል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0