ሱዳን የድህረ ጦርነት ፍኖተ ካርታ ይፋ አደረገች

ሰብስክራይብ
ሱዳን የድህረ ጦርነት ፍኖተ ካርታ ይፋ አደረገች በቅርቡ በአልጃዚራ እና ካርቱም በፈጥኖ ደራሽ ሃይል ሰራዊት ላይ የተመዘገበውን ድል የጠቀሰው የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ፍኖተ ካርታው የፖለቲካ ውይይት ለማስቀጠል፣ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት፣ ሕገ-መንግሥቱን ለማሻሻል እና ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ነው ብሏል። ከፍኖተ ካርታው ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ሽግግሩን እና የድህረ ጦርነት ግንባታን የመቆጣጠር ሀላፊነት የሚሸከም ገለልተኛ የባለሙያተኞች መንግሥት መመስረት እና ለፈጥኖ ደራሽ ሃይል የሚሰጡትን ድጋፍ ላነሱት ብሔራዊ ምክክር ማስጀመር ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም ፍኖተ ካርታው የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ እና የሲቪል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመረጥበትን ሂደት ዘርዝሯል። እንዲሁም ከፈጥኖ ደራሽ ሃይል ጋር ለሚደረግ የትኛውም ድርድር ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል። የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በቅድሚያ መሳሪያ ማውረድ፣ ከሲቪል ቦታዎች መልቀቅ፣ የኤል-ፋሸርን ከበባ ማንሳት እና ከዋና ዋና ቦታዎች መውጣት እንዳለባቸው በፍኖተ ካርታው ተገልጿል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0