"በዋሊያ አይቤክስ ብርቅየ እንስሳት ላይ የመጥፋት አደጋ ተጋርጧል" ሲል የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አስጠነቀቀ

ሰብስክራይብ
"በዋሊያ አይቤክስ ብርቅየ እንስሳት ላይ የመጥፋት አደጋ ተጋርጧል" ሲል የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አስጠነቀቀ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ከአፍሪካ ዋይልድ ላይፍ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር "የዋሊያ አይቤክስ ብሔራዊ ጥበቃ" በሚል መሪ ሃሳብ በጎንደር ከተማ ውይይት አካሂዷል። ለዋሊያ አይቤክስ የመጥፋት አደጋ የሕገ-ወጥ አደን መበራከት፣ ልቅ የሆነ ግጦሽ፣ ሕገ-ወጥ የቤት ግንባታ ዋነኛ ምክንያት ተደርገው በውይይቱ ተነስተዋል። በተጨማሪም የዋሊያ ቀንድ እና ጥፍር ለባሕላዊ መድኃኒትነት ያገለግላል በሚል፤ የዋሊያ አይቤክስ እንስሳትን ማደን እየተበራከተ መምጣቱን የሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ኀላፊ ማሩ ቢያድግልኝ ተናግረዋል። 865 ደርሶ የነበረው የዋሊያ አይቤክስ ቁጥር አሁን 306 መድረሱም ተገልጿል። ጥብቅ ቁጥጥር ካልተደረገ ብርቅየ እንስሳቱ ላይ የመጥፋት አደጋ ተጋርጧል ያለው የሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ  ፓርክ፤ ከባለ ድርሻ እና ከአጋር አካላት ጋር ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሠራ መግለጹን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0