የየካቲት 03 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የየካቲት 03 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስልጣን ያልተሰጠው የሰላም አስከባሪ ኃይል በዩክሬን የሚሰማራ ከሆነ፤ የሩሲያ ጦር ሕጋዊ ኢላማ ይሆናል ሲሉ በመንግሥታቱ ድርጅት የሩሲያ ቋሚ ተወካይ ቫሲሊ ኔቤንዚያ ለስፑትኒክ ተናገሩ። 🟠 የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት የዘረኝነት ውንጀላውን ተከትሎ አሜሪካዊው ስራ ፈጣሪ ኤለን መስክ የሀገሪቱን የሕግ ስርዓት እንዲያጠና መከሩ።🟠 ኪንሻሳ በምስራቃዊ ዲአርሲ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት የሉዋንዳ እና የናይሮቢ ሂደቶች እንደገና እንዲጀመሩ ጥሪ አቀረበች። 🟠 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በብረት እና በአሉሚኒየም የገቢ ምርቶች ላይ የ25% ቀረጥ ጣሉ።🟠 የሊቢያ ብሔራዊ አንድነት መንግሥት የእስራኤልን የፍልስጤም የመልሶ ሰፈራ ሃሳብ እንደ አደገኛ መካረር እንደሚቆጥረው ገለጸ። 🟠 የሩሲያ ዲፕሎማሲ የሩሲያን ትክክለኛ ሀገራዊ ጥቅም እንደሚያስጠብቅ እና ከአብዛኞቹ የዓለም ሀገራት ጋር ውጤታማ ግንኙነት እንደሚፈጥር ቭላድሚር ፑቲን የዲፕሎማት ቀንን ምክንያት በማድረግ ተናገሩ። 🟠 ትራምፕ ጋዛን በመግዛት የመልሶ ግንባታውን ሂደት እንዲያግዙ መሬቱን ከቀጣናው መንግሥታት ጋር ለማካፈል ዝግጁ ነኝ ማለታቸውን ሚዲያዎች ዘገቡ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0