ኢትዮጵያ የምስራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ማህበራት የምሥራቅ ኮንጎን ቀውስ ለመፍታት ያሳዩትን አመራር አወደሰች

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የምስራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ማህበራት የምሥራቅ ኮንጎን ቀውስ ለመፍታት ያሳዩትን አመራር አወደሰች በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረው የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ እና የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ የጋራ የመሪዎች ስብሰባ በታንዛንያ ዳሬ ሰላም ቅዳሜ እለት ተካሄዷል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የስብሰባውን የመጨረሻ ውጤት በመልካም ጎኑ እንደሚቀበል ገልጿል። የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ሀገራት መሪዎች የአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ እንዲያገኙ ያሳዩት ቁርጠኝነትና አጋርነት ምሳሌ የሚሆን ነው ሲልም ሚኒስቴሩ አክሏል፡፡ ስብሰባው በምሥራቅ ኮንጎ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም የሁለቱ ቀጣና ማህበራት የጦር አዛዦች በአምስት ቀናት ውስጥ ተገናኝተው የተኩስ አቁሙን ማስፈፀም የሚቻልበትን መንገድ እንዲዘይዱ አቅጣጫ አስቀምጧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0