ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የሰላም ስምምነት ለማካሄድ ሊሟሉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠች

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የሰላም ስምምነት ለማካሄድ ሊሟሉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠች ከኪዬቭ ጋር ሊደረጉ የሚችሉ የሰላም ስምምነቶች በዩክሬን ሕጋዊ መሪዎች መፈረም እንዳለባቸው፤ በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ ቋሚ ተወካይ ቫሲሊ ኔቤንዚያ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። የቮሎዲሚር ዘለንስኪ የፕሬዝዳንትነት ጊዜ ማብቃቱን ያስታወሱት ቋሚ ተወካዩ፤ የሥልጣን ጊዜው ካበቃ በኋላ ምርጫ እንዳልተደረገ ጠቁመዋል። በተጨማሪም ከሞስኮ ጋር ድርድር ማካሄድ የሚከለክለው እና በጥቅምት 2022 በዘለንስኪ የተፈረመው ሕግ፤ "የድርድሩን ሂደት እና ውጤት ሊያወሳስበው ይችላል" ሲሉ ዲፕሎማቱ ተናግረዋል። ኔቤንዚያ ሩሲያ "የጋራ ተቀባይነት ያለው የረዥም ጊዜ ዘላቂ ሰላም ለማግኘት ከሚፈልጉ ሁሉ ጋር" ለመነጋገር ሁሌም ዝግጁ ነች ብለዋል። ሆኖም የሰላም ስምምነቱን ማን ይፈርመዋል እንዴትስ ሕጋዊ ማድረግ ይቻላል የሚለው ጥያቄ መፍትሄ የሚያሻው እንደሆነ ጠቁመዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0