ታጣቂዎች በማሊ ጋኦ በጦር ሰፈር አቅራቢያ በፈፀሙት ጥቃት 25 ሲቪሎችን ገድለው 13 ማቁሰላቸውን የሀገሪቱ ጦር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
ታጣቂዎች በማሊ ጋኦ በጦር ሰፈር አቅራቢያ በፈፀሙት ጥቃት 25 ሲቪሎችን ገድለው 13 ማቁሰላቸውን የሀገሪቱ ጦር አስታወቀይህ ጥቃት ከጋኦ በ30 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘዉ የኮቤ መንደር አቅራቢያ የተፈፀመ ሲሆን አካባቢው የእስላሚክ ስቴት (ዳኤሽ)* እና ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች ችግር የሚፈጥሩበት ነው። ጦሩ በምላሹ 14 ታጣቂዎችን መግደሉን ያሳወቀ ሲሆን በጦሩ ላይ ስለደረሰው ጥቃት የተዘገበ ነገር የለም።በጎርጎሮሳዊያኑ 2012 በቱአሬግ አማጺያኝን አነሳሽነት ወደ አመፅ የገቡት እስላማዊ ታጣቂዎች፤ ከሰሜን ማሊ በመነሳት በሳህል ቀጠና መጠነሰፊ ሁከት በመፍጠር በሺዎች የገደሉ ሲሆን በሚሊየኖች የሚቆጠሩትን አፈናቅለዋል።* በሩሲያ እና በብዙ ሀገሮች የታገደ አሸባሪ ቡድንበእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0