በኢትዮጵያ የተከፈተው አዲስ የፕላስቲክ ፎርምወርክ ፋብሪካ በዓመት ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት የሚችል መሆኑ ተገለጸበስምንት ሚሊዮን ዶላር የተገነባውን የፎርምወርክ ፋብሪካ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል መርቀውታል። ሚኒስትሩ በምርቃቱ ወቅት እንደተናገሩት መንግሥት ለአምራቹ ዘርፍ ትኩረት በመስጠት የፖሊሲ እና ለኢኮኖሚ እድገት የሚያግዙ የህግ ማእቀፍ ማሻሻያዎችን ያደረገ ሲሆን፤ ይህም ምርታማነትን እና ዘላቂ ልማትን መደገፍ ያካትታል ብለዋል።ሚኒስትሩ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን በማልማት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት እንዲሁም የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ ከእንጨት እና ከብረት የሚሰሩ ፎርምወርኮችን በፕላስቲክ በመቀየር መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።የኤችኬ ንግድ ቡድን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ካሳነሽ አያሌዉ እንዳስታወቁት ድርጅታቸው በድጋሚ አገልግሎት ላይ የሚውል የፕላስቲክ ፎርምወርክ ምርት ለሀገረ ውስጥ እና የውጭ ገበያዎች አምርቶ ለማቅረብ ዝግጁ ነው። ለዚህም አገልግሎት ከቻይና እና ከአደጉ ሀገራት ቴክኒዎሎጂዎችን ማስገባታቸውን ተናግረዋል። ዋና ስራ አስኪያጇ ፎርምወርክ ከ20 -25 በመቶ የሚሆነውን የግንባታ ወጪ እንደሚወክል በመግለፅ፤ ፋብሪካው የሀገር ውስጥ እና የጎረቤት ሀገራትን የፎርምወርክ ፍላጎት በሚያሟላበት አቋም ላይ መሆኑን ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በኢትዮጵያ የተከፈተው አዲስ የፕላስቲክ ፎርምወርክ ፋብሪካ በዓመት ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት የሚችል መሆኑ ተገለጸ
በኢትዮጵያ የተከፈተው አዲስ የፕላስቲክ ፎርምወርክ ፋብሪካ በዓመት ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት የሚችል መሆኑ ተገለጸ
Sputnik አፍሪካ
በኢትዮጵያ የከፈተው አዲስ የፕላስቲክ ፎርምወርክ ፍብሪካ በየአመቱ ወደ ውጭ ይወጣ የነበረ 15 ሚሊዩን ዶላር ይቆጥባል ተባለይህ በስምንት ሚሊዩን ዶላር የተገነባውን የፎርምወርክ (ለግንባታ ሆነ ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል ምርት) ፍብሪካ የኢንዱስትሪ... 09.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-09T11:24+0300
2025-02-09T11:24+0300
2025-02-10T10:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በኢትዮጵያ የተከፈተው አዲስ የፕላስቲክ ፎርምወርክ ፋብሪካ በዓመት ከ15 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት የሚችል መሆኑ ተገለጸ
11:24 09.02.2025 (የተሻሻለ: 10:14 10.02.2025)
ሰብስክራይብ