በዶንዬትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ በማኬዬቭካ የዩክሬን ሀይሎች የፈፀሙት ጥቃት ሌላ አስነዋሪ ወንጀል ነው በማለት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
በዶንዬትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ በማኬዬቭካ የዩክሬን ሀይሎች የፈፀሙት ጥቃት ሌላ አስነዋሪ ወንጀል ነው በማለት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህንን የዩክሬን ጥቃት እንደ ሽብር ጥቃት ይቆጥረዋል ፤ የምእራባውያን ሀገሮች ባለስልጣናትም ሀላፊነት አለባቸው በማለት ማሪያ ዛክህሮቫ ተናግረዋል። ቃልአቀባይዋ ፤ የኬቭ አገዛዝ " ሰብአዊነት የጎደለው የናዚ ባህሪ ያለው አስነዋሪ ፣ የደም ወንጀል መፈፀሙን" አሳይቷል ብለዋል። ሩሲያ ሀላፊነት የሚሰማቸው መንግስታት እና የሚመለከታቸው አለምአቀፍ ተቋማት ይህንን ጥቃት እንዲያወግዙት ጥሪ አቅርባለች። ይህ በሩሲያ ክልሎች ውስጥ ህዝብ በሚበዛባቸው  አካባቢዎች የተፈፀሙ የቦምብ ጥቃቶች እና የሰላማዊ ሰዎች ግድያ የቮሎዶምየር ዜሌንስኪ አገዛዝ አስከፊነት ማረጋጋጫ ነው በማለት ባለስልጣኗ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0