ከሳምንት በኋላ የሚካሄደውን 38ተኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከ1 ሺህ በላይ ጋዜጠኞች ሽፋን ይሰጡታል ተባለ

ሰብስክራይብ
ከሳምንት በኋላ የሚካሄደውን 38ተኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከ1 ሺህ በላይ ጋዜጠኞች ሽፋን ይሰጡታል ተባለየኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን እንዳስታወቀው ፤ መጪውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት የተወጣጡ ከ 1ሺህ በላይ ጋዜጠኞች ሽፋን እንዲሰጡ በቂ ዝግጅት ተደርጓል። የ'ፕሬስ ይለፍ' በማዘጋጀት የመዳረሻ የቪዛ አገልግሎት በቀልጣፍ ሁኔታ እየተሰጠ ነዉ። በአዲስ አበባ የሚካሄደውን ጉባኤ ለመዘገብ 390 የሀገር ውስጥ እና 530 የውጭ ሀገር ጋዜጠኞች ተመዝግበዋል ያለው ባለስልጣኑ ፤ በተለይም የውጭ ሀገር ጋዜጠኞች መጠቀሚያ እቃዎቻቸውን ይዘው ሲገቡ ፤ ከቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ ኤርፖርት ጉምሩክ ፣ ከአፍሪካ ህብረት ባጅ ማእከል እና ከባለስልጣኑ  በተወጣጡ ባለሙያዎች 24 በቂ የሆነ አገልግሎት እያገኙ መሆኑ ጨምሮ ገልጿል። የመሪዎቹ ጉባኤ የካቲት ስምንት እና ዘጠኝ በህብረቱ መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል። የስፑቲኒክ ባልደረቦችም ይህንኑ ጉባኤ ከቦታው ለመዘገብ ዝግጅታቸውን  ጨርሰዋል።የጉባኤውን ውሎ ከስፑትኒክ ኢትዮጵያ ይከታተሉ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0