የሩሲያው የሰብአዊ ደህንነት እንባጠባቂ የተላላፊ በሽታዎች ተንቀሳቃሽ ቤተ ሙከራ ለኮንጎ አስተላለፈ

ሰብስክራይብ
የሩሲያው የሰብአዊ ደህንነት እንባጠባቂ የተላላፊ በሽታዎች ተንቀሳቃሽ ቤተ ሙከራ ለኮንጎ አስተላለፈ " ይህ በሮስፖትሬብናድዞር የተበረከተው ተንቀሳቃሽ ቤተ ሙከራ በሩሲያ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተሞላ እና የኮንጎ ሪፐብሊክን የቤተ ሙከራ መሰረተ ልማት የሚያሳድግ ነው። ይህ ቤተ-ሙከራ በርቀት ቦታዎች እና ኢንፌክሽን በተከሰተባቸው ቦታዎች የሚገኙ በጣም አደገኛ ተላላፊ በሽታዎችን ለማከም እገዛ ያደርጋል" በማለት መግለጫው አስነብቧል።ይህ የቤተ ሙከራ ርክክብ የሩሲያ - ኮንጎ በተላላፊ በሽታዎች ላይ ያላቸውን ትብብር አካል መሆኑን ይፋ ተደርጓል። ባለፉት ሁለት አመታት ከተላኩ የተላላፊ በሽታዎችን የመለየት እና ለመመርመር የሚያግዙ የቤተ ሙከራ ቁሳቁሶች ክልሉን በማከለ መልኩ የተላለፈ ሲሆን ፤ በተጨማሪ ከ60 በላይ የኮንጎ እስፔሻሊስቶች ስልጠና ወስደዋል። " በተያዘው የጎርጎሮሳውያን አዲስ አመት ተጨማሪ 50 እስፔሻሊስቶች በሩሲያ የተላላፊ በሽታዎችን መከላከል እና ምላሽ አሰጣጥ ላይ ስልጠና ይወስዳሉ። በተጨማሪም ፤ ሮስፖትሬብናድዞር በኮንጎ ካሉ አጋሮቹ ጋር  አደገኛ እና በአፍሪካ ውስጥ በብቸኝነት ስለሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎች ፤ በምሳሌነትም በህፃናት እና በአዋቂዎች ላይ ስለሚታይ አደገኛ ተቅማጥ ተከታታይ የሆነ ሳይንሳዊ ጥናት ያደርጋል " በማለት መግለጫው አጠቃሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0