ካሳ ላይ ትኩረቱን የሚደርገው መጪው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ፤ አፍሪካ የወደፊት ተግዳሮቶቿ ላይ ስትራቴጂካዊ ድል እንድታስመዘግብ ጥሩ እድል ይፈጥራል ሲሉ የኢትዮጵያ ተወካይ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ካሳ ላይ ትኩረቱን የሚደርገው መጪው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ፤ አፍሪካ የወደፊት ተግዳሮቶቿ ላይ ስትራቴጂካዊ ድል እንድታስመዘግብ ጥሩ እድል ይፈጥራል ሲሉ የኢትዮጵያ ተወካይ ተናገሩ ''የማካካሻ ፍትህ ለአፍሪካውያን እና ለዘረ አፍሪካውያን'' በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው መጪው 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ፤ በተለይ የተኩስ ድምጽን ማጥፋት እና የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ እድገት በማፋጠን ረገድ ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ፤ ለስኬታማ የወደፊት ዘመን ስትራቴጂ ለመንደፍ እድል ይሰጣል ሲሉ በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ምክትል ተወካይ ነብዩ ተድላ ለኢዜአ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከየካቲት 9 እስከ 10 በአዲስ አበባ ለሚካሄደው ጉባዔ በቂ ዝግጅት እንዳደረገች እና የጉባዔው የመጨረሻ ውጤት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እንዲያንጸባርቅ የተሰሩ ስራዎች እየተጠናቀቁ እንደሆነም ጠቁመዋል። የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በቅኝ ግዛት፣ ባርነት እና አፓርታይድ የተፈጠሩ ታሪካዊ ኢፍትሃዊ ድርጊቶችን በፈውስ፣ ፍትሃዊነት እና ለአፍሪካ መብቶች እና አስተዋፅኦዎች እውቅና በመስጠት ለመቅረፍ፤ ለአፍሪካ የካሳ አጀንዳ ድጋፍ ለማሰባሰብ ያለመ ነው። የሀገር መሪዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት እና ከፍተኛ ልዑካን በመገኘት የአፍሪካን መፃኢ እድል በሚወስኑ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0