የሱዳን ጦር ማእከላዊ ካርቱምን ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል መልሶ ለመቆጣጠር ከባድ የሆነ ጥቃት መክፈቱ ተዘገበ

ሰብስክራይብ
የሱዳን ጦር ማእከላዊ ካርቱምን ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል መልሶ ለመቆጣጠር ከባድ የሆነ ጥቃት መክፈቱ ተዘገበ በትላንትናው እለት የሱዳን ጦር  የሀገሪቱን መዲና ካርቱምን ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል ለመቀማት ዘርፈብዙ ጥቃት ከፍቷል ፤ በማለት የጦሩ ምንጮች ለፈረንሳይ ሚዲያ ተናግረዋል። ምንጮቹ ጨምረውም ጦሩ ወደ ማእከላዊ የከተማዋ ክፍል እየደረሰ መሆኑን እና በሞሀመድ ሃምዳን ደጋሎ የሚመራውን የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ከከተማዋ የማባረር እቅድ እንዳለው ተናግረዋል። "የሱዳን ጦር ወደ ማእከላዊ ካርቱም እየደረሰ ነው ፤ እናም የደጋሎን ታጣቂዎች እናባርራቸዋለን። የጦር ኃይላችን ከብዙ አቅጣጫዎች እየገፋ ነው" በማለት ምንጩ ተናግሯል። ጦሩ ከማእከላዊ ካርቱም ወደ ኦምዱርማን ከተማ የሚወስደውን እስትራቴጂካዊ መንገድ ተቆጣጥሮታል ፤ ይህም የታላቋ ካርቱም ቁልፍ ክፍል ነው በማለት ሪፖርቱ ዘግቧል፤ አክሎም  እያካሄደ ባለው መጠነሰፊ ኦፕሬሽን አማካኝነት ፤ ከምስራቅ ሱዳን የተነሱ ወታደሮች የደቡብ ዋና መቀመጫ ከሆነችው ከአል -ጃዚራ ግዛት ጋር ግንኙነት ለመፍጠር በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛሉ ።የካርቱም የደቡብምሥራቅ መግቢያ በሆነው ሶባ ድልድይ አካባቢ ግጭቶች እንዳሉ ተዘግቧል።"ጦራችን ካርቱም ውስጥ ወሳኝ የሆነ አካሄድ  እያሳየ ነው ፤ ከፈጥኖደራሹ ኃይል የሪፐብሊካን ቤተመንግስት በሶስት ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኘውን የአል -ሩማላን አካባቢ ሙሉ በሙሉ  የተቆጣጠረ ሲሆን ፦  የመድሀኒት ማጠራቀሚያ ፣ የኢንዱስትሪ አካባቢ እና የሀገሪቱ ገንዘብ ማምረቻ በስፍራው ይገኛሉ" በማለት የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ናቢል አብዳላህ በትላንትናው እለት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0