ኋይት ሀውስ 97 በመቶ የዩኤስኤድ ሰራተኞችን ሊያሰናብት መሆኑ ተሰማ

ሰብስክራይብ
  ኋይት ሀውስ 97 በመቶ የዩኤስኤድ ሰራተኞችን ሊያሰናብት መሆኑ ተሰማየአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፤ በመላው አለም 10,000 ሰራተኞች የነበረውን የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤድ ወደ 294 ለመቀነስ ማሰባቸውን ምእራባውያን ሚዲያዎች ምንጮችን ጠቅሰው ዘግበዋል።ዩኤስኤድ ከዛሬ ጀምሮ በመላው አለም የሚገኙ ሰራተኞች በድርጅቱ በቀረበላቸው አስገዳጅ እረፍት መሰረት ከስራ ቦታቸው እንደተሰናበቱና አስፈላጊ ያልሆኑ ኮንትራቶችም መቋረጣቸውን ገልጿል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ማርክ ሩቢዮን የዩኤስኤድ ተጠባባቂ ሀላፊ አድርገው ያለፈው ሰኞ ሾመዋል። ሩቢዮ የዩኤስኤድ የውጭ እርዳታ እንቅስቃሴዎች እየተገመገመ መሆኑን እና በእርግጠኝነት የመልሶ ማዋቀር ስራ እንደሚኖር ለኮንግረስ አስታውቀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0