ተመድ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ የሰላም ጥሪ እና አለም አቀፍ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረበ

ሰብስክራይብ
ተመድ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ የሰላም ጥሪ እና አለም አቀፍ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረበሁኔታውን አስመልክቶ ተጨማሪ ሀሳቦች፦⏺ ተመድ ለሰላም ጥሪ አቀረበ፤ የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቀውሱን አስመልክቶ በታንዛንያ እና በኢትዩጵያ ከሚካሄዱት ጉባኤዎች አስቀድሞ በኮንጎ ያለሁ ሁከት እንዲቆም ጠይቀዋል። የኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሌክስ ሺሴኬዲ እየተካሄደ ያለውን ግጭት አስመልክቶ በዛሬው እለት በታንዛኒያ ዳሬሰላም ሚደረገው የምስራቅና እና የደቡብ አፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ⏺ የኤም23 ግስጋሴ፤ የኤም23 አማፂ ቡድን የአይሁሲ ከተማን የተቆጣጠሩ ሲሆን በደቡብ ኪቩ ወሳኝ የሆነውን የብካቩ አየር ማረፊያን ለመቆጣጠር ተቃርበዋል። ⏺ የሉአላዊነት ስጋት፤ ጉቴሬስ እየተካሄደ ባለው ግጭት የኮንጎ ግዛት አንድነት እና ሉአላዊነት እንዲከበር በአፅንኦት ጠይቀዋል።⏺ የሩዋንዳ ጦር ጥቃት፤ በምስራቅ ኮንጎ የሩዋንዳ ጦር በጎርጎሮሳዊያኑ የጥር ወር ፈፅሞታል በተባለ ጥቃት ከ 3,000 ሰዎች በላይ ሲሞቱ ሌላ 3,000 ያህል የመቁሰል አደጋ አጋጥሟቸዋል፤ የእውነተኛ ተጎጂዎች ቁጥር ከዚህ ይበልጣል።⏺ በክልሉ የአደጋ መስፋፋት ስጋት፤ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ሀላፊ እየተካሄደ ያለው ሁከት ከኮንጎ የማለፍ  ስጋት "የአሁንን ያህል ከፍተኛ" ሆኖ አያውቅም።⏺ አለም አቀፍ ምርመራ፤ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በምስራቅ ኮንጎ እየተካሄደ ያለውን ሁከት አስመልክቶ ምርመራ ለማድረግ መወሰኑን አስታውቋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0