ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገሮች ጋር ያላትን አጋርነት እና የኢኮኖሚያዊ ትብብርን ማጠናከርን ቅድሚያ እንደምትሰጠው የፕሬዝዳንቱ አማካሪ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገሮች ጋር ያላትን አጋርነት እና የኢኮኖሚያዊ ትብብርን ማጠናከርን ቅድሚያ እንደምትሰጠው የፕሬዝዳንቱ አማካሪ ተናገሩ" በሩሲያ እና አፍሪካ ሀገሮች መሀከል እያደገ ያለው የአጋርነት ግንኙነት አሁን ላይ የሀገራችን አመራር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው" ሲሉ የሩሲያ ፕሬዝዳንት አማካሪ አንቶን ኮብያኮቭ ተናገሩ ። አማካሪው ይህንን ያሉት  የአፍሪካ ሀገሮች  የኢኮኖሚ አቀናጅ ኮሚቴ (አፍሪኮም) ሊቀመንበር ከሆኑት ኢጎር ሞሮዞቭ ጋር በነበራቸው የጎርጎሮሳውያኑ 2024 የሩሲያ - አፍሪካ ፎረም ዉጤት እና 2025 እቅዶችን በተወያዩበት ወቅት ነው። ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በሁሉም ዘርፍ ለመወያየት ዝግጁ ናት ፤ እንዲሁም በጋራ ለሚሰሩ የቢዝነስ ኩነቶች የሩሲያ እና አፍሪካን ትብብር ያጠናክረዋል ፤ በማለት የሩሲያ- አፍሪካ አጋርነት ፎረም አዘጋጅ ኮሚቴ ዋና ፀሀፊ የኮብያኮቭ ተናግረዋል። " በጎርጎሮሳዊያኑ 2025 ፤ ሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገሮች በፎረሙ ላይ በአንድነት የሚሰሩ ይሆናል። ይህ ኩነት  የሚደረገው በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በሚገኙ አጋሮቻችን ተሳትፎ ፤ አግባብነት እና ብቃት  እየተመሰረተ ባለው የቢዝነስ ግንኙነቶች እንዲሁም እያደገ ያለው የጋራ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ  እና ባህላዊ ፕሮጀክቶች አማካኝነት ነው " በማለት የአፍሪኮም ሊቀመንበር  ሞሮዞቭ ጠቁመዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0