ክሬምሊን የዩክሬን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ጥያቄ ለእብደት የተቃረበ ነው አለ

ሰብስክራይብ
ክሬምሊን የዩክሬን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ጥያቄ ለእብደት የተቃረበ ነው አለ "በአጠቃላይ እንደዚህ አይነት ንግግሮች...ለእብደት የቀረቡ ናቸው። እውነታው የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ስርጭት ላይ ክልከላ የሚያስቀምጡ ስርዓቶች እና የመሳሰሉት መኖራቸው ነው" ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። በዩክሬን ቀውስ ዙርያ በክሬምሊን የተሰጡ ተጨማሪ መግለጫዎች፦ ሞስኮ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ወደ ኪየቭ ለማዘዋወር የሚደረግ ውይይት የእብደት እና አደገኛ መሆኑን የሚረዱ የአውሮፓ ፖለቲከኞች እንዳሉ ተስፋ ታደርጋለች። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዘሌንስኪን እንደ ጠላት ይመለከቱታል በሚለው ጉዳይ ዙርያ ስሜታዊነት ቦታ ሊኖረው አይችልም። ዘሌንስኪ ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ ነኝ ብለው ለሰጡት አስተያየት ምላሽ የሰነዘሩት የክሬምሊን ቃል አቀባይ፤ ለድርድር ዝግጁነት በአንድ ነገር ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት፤ አለበለዚያ አስተያየቶቹ ባዶ ቃላቶች ናቸው ብለዋል። የልዩ ወታደራዊ ዘመቻው አሁናዊ ሁኔታ ለእንደዚህ ዓይነቱ ድርድር ፍላጎት ማሳየት ያለባት ኪዬቭ እንደሆነች ያመለክታል። በሰው ሰራሽ አስተውህሎት (AI) የመነጨ ገላጭ ምሥልበእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0