በጦርነት የተገደሉ ከ2,000 በላይ ሰዎች በምስራቅ ኮንጎ ጎማ ከተማ አቅራቢያ እንደተቀበሩ ተሰማ "የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናት ከ2,000 በላይ አስከሬኖች እንደተቀበሩ ነግረውኛል። ይህ የግድያውን መጠን ያሳያል" ሲሉ የኮንጎ መንግሥት ቃል አቀባይ ፓትሪክ ሙያያ ለአንጎላ ኤጀንሲ አንጎፕ ተናግረዋል። ሙያያ እንዳሉት ቁጥሩ በጅምላ መቃብር የተቀበሩትን አይጨምርም። የኮንጎ መንግሥት የጠላትን "ተጠያቂነት ለማረጋገጥ"፤ ሩዋንዳ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግዛት ውስጥ የምትፈፅመውን የጦር ወንጀል እመዘገበ እንደሚገኝም አክለዋል። በተጨማሪም የጎማ ሆስፒታሎች በቆሰሉ ሰዎች እንደተጨናነቁ እና አስከሬኖች በጎዳና ላይ ወድቀው እንደሚገኙ፤ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ገልጿል። "የሬሳ ቤቶች ሞልተዋል፤ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች በተጎዱ ሰዎች ተጨናንቀዋል" ሲል በመግለጫው አስታውቋል። የሰብዓዊ ድርጅቶች "በመጋዘኖቻቸው ላይ የደረሰው ዘረፋ የሚፈጥረውን ተፅእኖ መገምገማቸውን ቀጥለዋል።" "በጎማ እና ዘርያው የእርዳታ አቅርቦቱን ለማስቀጠል" ጥረት እያደረጉም ነው ተብሏል። ውሀን በክሎሪን ለማከም ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፤ የጎማ ነዋሪዎች በተፈጠረው እጥረት ሳቢያ ከኪቩ ሀይቅ ያልታከመ ውሃ ለመጠቀም እንደተገደዱ ተገልጿል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በጦርነት የተገደሉ ከ2,000 በላይ ሰዎች በምስራቅ ኮንጎ ጎማ ከተማ አቅራቢያ እንደተቀበሩ ተሰማ
በጦርነት የተገደሉ ከ2,000 በላይ ሰዎች በምስራቅ ኮንጎ ጎማ ከተማ አቅራቢያ እንደተቀበሩ ተሰማ
Sputnik አፍሪካ
በጦርነት የተገደሉ ከ2,000 በላይ ሰዎች በምስራቅ ኮንጎ ጎማ ከተማ አቅራቢያ እንደተቀበሩ ተሰማ "የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናት ከ2,000 በላይ አስከሬኖች እንደተቀበሩ ነግረውኛል። ይህ የግድያውን መጠን ያሳያል" ሲሉ የኮንጎ መንግሥት ቃል አቀባይ... 05.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-05T15:39+0300
2025-02-05T15:39+0300
2025-02-05T16:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በጦርነት የተገደሉ ከ2,000 በላይ ሰዎች በምስራቅ ኮንጎ ጎማ ከተማ አቅራቢያ እንደተቀበሩ ተሰማ
15:39 05.02.2025 (የተሻሻለ: 16:14 05.02.2025)
ሰብስክራይብ