ኢትዮጵያ እና ኬንያ የሸኔ ታጣቂ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ ማካሄድ ጀመሩ ዘመቻው የሁለቱ ሀገራት የጸጥታ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ካካሄዱት የጋራ የውይይት መድረክ በኋላ የመጣ ነው። ዘመቻው በሽብርተኝነት፣ የኮንትሮባንድ ንግድ፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች እና የመሣሪያ ዝውውር ላይ የሚሳተፈውን የሸኔ ታጣቂ ቡድን፤ ከሁለቱ ሀገራት ድንበሮች አካባቢ ለማስወገድ ያለመ እንደሆነ፤ የኢትዮጵያ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል። የሁለቱ ሀገራት የደኅንነትና የጸጥታ አካላት በየድንበራቸው ውስጥ በሚገኙ የቡድኑ ካምፖች ላይ የተቀናጀ ዘመቻ እያካሄዱ እንደሚገኙ ተገልጿል።የተጀመረው የተቀናጀ ዘመቻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋገጠው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መረጃ፤ ለሸኔ ታጣቂ ቡድን የቀረበው የሰላም መንገድ አሁንም ክፍት መሆኑን ጠቁሟል፡፡ ቀሪዎቹ የቡድኑ አባላትም የቀረበላቸውን የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ ጥሪ መቅረቡን፤ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱን ጠቅሶ የመንግሥት ሚዲያ ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዮጵያ እና ኬንያ የሸኔ ታጣቂ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ ማካሄድ ጀመሩ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ የሸኔ ታጣቂ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ ማካሄድ ጀመሩ
Sputnik አፍሪካ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ የሸኔ ታጣቂ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ ማካሄድ ጀመሩ ዘመቻው የሁለቱ ሀገራት የጸጥታ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ካካሄዱት የጋራ የውይይት መድረክ በኋላ የመጣ ነው። ዘመቻው በሽብርተኝነት፣ የኮንትሮባንድ ንግድ፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች እና... 05.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-05T12:04+0300
2025-02-05T12:04+0300
2025-02-05T12:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий