38ኛውን የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ካለፉት ጊዚያት በላቀ ደረጃ ለማስተናገድ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ

ሰብስክራይብ
38ኛውን የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ካለፉት ጊዚያት በላቀ ደረጃ ለማስተናገድ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የዘንድሮ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እየተደረገ ያለውን ዝግጅት የተሳታፊ ሀገራት ቀዳሚ ልዑካን ቡድን አባላት ጎብኝተዋል።  የቡድኑ አባላት በጉብኝታቸው፤ ብሔራዊ ቤተመንግሥት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የክብር ሳሎን፣ አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ሴንተር እና የአፍሪካ ሕብረት ዋና መሥሪያ ቤትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አዚዛ ገለታ፤ ጉብኝቱ ለጉባኤው ኢትዮጵያ እያደረገች ስላለው ዝግጅት ተሳታፊ ሀገራት በቂ መረጃ እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል።  ለዘንድሮው የሕብረቱ ጉባኤ ኢትዮጵያ በላቀ ደረጃ ዝግጅት በማድረግ የተሳካ መስተንግዶ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተር ጄነራሏ ተናግረዋል።  መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0