የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ የሳልቫዶር ፕሬዝዳንት አሜሪካውያንን ጨምሮ ወንጀለኞችን ለመቀበል ሃሳብ ማቅረባቸውን ገለፁ

ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ የሳልቫዶር ፕሬዝዳንት አሜሪካውያንን ጨምሮ ወንጀለኞችን ለመቀበል ሃሳብ ማቅረባቸውን ገለፁ "በሀገራችን በእስር ላይ የሚገኙትን አደገኛ አሜሪካዊያን ወንጀለኞችን፤ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን እና ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸውን ጨምሮ፤ በእስር ቤት ለማቆየት ሃሳብ አቅርበዋል" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከኤል ሳልቫዶር መሪ ጋር ከተወያዩ በኋላ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። የኤል ሳልቫዶር ፕሬዝዳንት ናይብ ቡኬሌ የሁለቱ ሀገራት መንግሥታት የስደተኞችን ቀውስ ለመቅረፍ “ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ” ስምምነት ላይ ለመድረስ እንደተቃረቡ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል። ፕሬዝዳንቱ ስምምነቱ በዩናይትድ ስቴትስ እና በኤል ሳልቫዶር መካከል ብቻ ሳይሆን ከሌሎች የላቲን አሜሪካ ሀገራት ጋር ተደርጎ የማይታወቅ በታሪክ የመጀመሪያው ነው ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0