ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የቪዛ ችግሮችን ለመቅረፍ ተስማሙ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የቪዛ ችግሮችን ለመቅረፍ ተስማሙ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ እና የደቡብ ሱዳን የዜግነት፣ ፓስፖርት እና ኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ሳይመን ማጁር ፓቤክ ከቪዛ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። አምባሳደር ነቢል በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከቪዛ እና መኖሪያ ፈቃድ ጋር በተያያዘ እየገጠማቸው ያለው ችግር እንዲቀረፍ በውይይቱ ወቅት ጠይቀዋል። ዳይሬክተር ጄኔራል ሳይመን ማጁር ፓቤክ በበኩላቸው የቪዛና የመኖሪያ ፍቃድ ጉዳዮችን ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር በመነጋገር ለመፍታት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። በውይይቱ በደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከቪዛ፣ መኖሪያ ፈቃድና አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ መፍትሄ ማግኘት በሚችሉበት መንገድ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ እንደተደረሰ ጁባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0