የሴኔጋል መንግሥት ከ2021 እስከ 2024 በሀገሪቱ በተከሰተው ብጥብጥ ለተጎዱ ቤተሰቦች የሚከፋፈል 15፣600 ዶላር ካሳ መደበ

ሰብስክራይብ
የሴኔጋል መንግሥት ከ2021 እስከ 2024 በሀገሪቱ በተከሰተው ብጥብጥ ለተጎዱ ቤተሰቦች የሚከፋፈል 15፣600 ዶላር ካሳ መደበ ውሳኔውን የሴኔጋል የቤተሰብ እና የአንድነት ሚኒስትር ማይሙና ዲዬ በሴኔጋል ፕሬስ ድርጅት በተለቀቀ ቪዲዮ አስታውቀዋል። እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ 79 የሟች ቤተሰቦች ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች እንክብካቤ፣ የጤና አገልግሎት እና የማህበራዊና የጤና ድጋፍ ያገኛሉ። በተጨማሪም በሁከቱ የተያዙ እና የተጎዱ ከ2፣000 በላይ ሰዎች እያንዳንዳቸው 780 ዶላር ይደርሳቸዋል።   መንግሥት በብጥብጥ ጉዳት የደረሰባቸውን ለመካስ በድምሩ 7.8 ሚሊዮን ዶላር መድቧል። በቀድሞው ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል እና በተቃዋሚያቸው የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦስማን ሶንኮ መካከል በተፈጠረው የፖለቲካ ውጥረት፤ ከ2021 እሰከ 2024 በሴኔጋል ከፍተኛ ብጥብጥ ተነስቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0