ዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ትብብሩን በማጠናከር የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት ለማጠናከር እንደሚሰራ ገለፀ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የተሳተፉት የዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ጠቅላይ ምክር ቤት ቢሮ አባል እና የሩሲያ ፌዴሬሽን ሴናተር አንድሬ ክሊሞቭ፤ ማክሰኞ እለት ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ኢትዮጵያና ሩሲያ ጠንካራ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን አጋርነት እንዳላቸው በመግለጫቸው ያነሱት ክሊሞቭ፤ በጉባዔው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከሌሎች የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ስኬታማ ውይይቶች ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ውይይቶቹ የፓርቲ ለፓርቲ ትብብር እና የሀገራቱን ሁለትዮሽ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙርያ ያተኮሩ እንደነበር አመላክተዋል። ሴናተር አንድሬ ክሊሞቭ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችንም ያደነቁ ሲሆን አዲስ አበባ ተለውጣ እና ውብ ገፅታ ተላብሳ መመልከታቸውን ገልጸዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ትብብሩን በማጠናከር የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት ለማጠናከር እንደሚሰራ ገለፀ
ዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ትብብሩን በማጠናከር የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት ለማጠናከር እንደሚሰራ ገለፀ
Sputnik አፍሪካ
ዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ትብብሩን በማጠናከር የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት ለማጠናከር እንደሚሰራ ገለፀ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የተሳተፉት የዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ጠቅላይ ምክር ቤት ቢሮ አባል እና የሩሲያ ፌዴሬሽን... 04.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-04T10:50+0300
2025-02-04T10:50+0300
2025-02-04T11:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ትብብሩን በማጠናከር የሁለቱን ሀገራት ግኑኝነት ለማጠናከር እንደሚሰራ ገለፀ
10:50 04.02.2025 (የተሻሻለ: 11:14 04.02.2025)
ሰብስክራይብ