ደቡብ አፍሪካ ትራምፕ እርዳታ ሊያቋርጡ እንደሚችሉ ማስፈራራታቸውን ተከትሎ የመሬት ወረሳ ፖሊሲዋን ተከላከለች

ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ ትራምፕ እርዳታ ሊያቋርጡ እንደሚችሉ ማስፈራራታቸውን ተከትሎ የመሬት ወረሳ ፖሊሲዋን ተከላከለች የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ ሀገሪቱን "በመሬት ነጠቃ እና የተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በመበደል" በመክሰስ፤ ከተሟላ ምርመራ በኋላ እርዳታ ለማቋረጥ መዛታቸው ተከትሎ፤ የመሬት ወረሳ ሕጉ የተለየ አይደለም ሲል የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ተከላክሏል። የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ምላሽ፤ የመሬት ወረሳ ሕጉ ያልተለመደ ሳይሆን የሕገ-መንግስታዊ ዲሞክራሲ አካል እንደሆነ አአስረግጧል። የትራምፕ አማካሪዎች “የምርመራ ጊዜውን” በመጠቀም “በሀገሪቱ ፖሊሲዎች ላይ የተሟላ ግንዛቤ” እንደሚያገኙም ተስፋውን ገልጿል። "ይህ አካሄድ ሀገሪቱ ለዲሞክራሲያዊ እሳቤዎች እና አስተዳደር ዋጋ እና እውቅና እንደምትሰጥ በመረጃ ላይ የተመሰረተ እይታን ለማግኘት ይረዳል። በርካታ ሀገራት ተመሳሳይ ሕግ ስላላቸው፤ የወረሳ ሕጋችን የተለየ እንዳልሆነ ግልጽ ሊሆን ይችላል" ሲል ሚኒስቴሩ አክሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0