የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዩክሬን በሱድዛ አዳሪ ትምህርት ቤት ላይ ያካሄደችውን ጥቃት እንዲያወግዝ ሩሲያ ጠየቀች

ሰብስክራይብ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዩክሬን በሱድዛ አዳሪ ትምህርት ቤት ላይ ያካሄደችውን ጥቃት እንዲያወግዝ ሩሲያ ጠየቀች የሩሲያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ታቲያና ሞስካልኮቫ ተመድ እና የአውሮፓ ምክር ቤትን ጨምሮ፤ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዩክሬን በኩርስክ ክልል በሚገኘው ሱድዛ አዳሪ ትምህርት ቤት ላይ የፈፀመችውን ጥቃት እንዲያወግዙ ጠይቀዋል። የዩክሬን ጦር በጥር 24 ቀን ኩርስክ ክልል ውስጥ በዩክሬን በተያዘው የሱድዛ ከተማ የሲቪል መሠረተ ልማቶችን ሆን ብሎ እንዳጠቃ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። ጥቃቱ ኪዬቭ በሩስኮዬ ፖርችኖዬ መንደር ከምትፈፅመው ግፍ ዓለምን ለማዘናጋት ያካሄደችው ነው ሲል ሚኒስቴሩ ተናግሯል። አክሎም “በሲቪል ተቋማት ላይ የተደረገው ጥቃት በኪዬቭ ስልጣን ላይ ያሉቱን የአሸባሪነት እና ኢሰብዓዊነት የጎደለው ድርጊት በድጋሚ ያሳያል" ብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0