ሩዋንዳ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭት ዙርያ የሚካሄደውን አህጉራዊ ስብሰባ እንደምትደግፍ ገለፀች

ሰብስክራይብ
ሩዋንዳ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግጭት ዙርያ የሚካሄደውን አህጉራዊ ስብሰባ እንደምትደግፍ ገለፀች የደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ (ሳድክ)፤ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ያለውን የጸጥታ ችግር ለመቅረፍ ከምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ጋር የጋራ ስብሰባ ለማካሄድ ጥሪ አቅርቧል። የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሃሳቡን እንደሚቀበል በመግለፅ፤ ለግጭቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ በድጋሚ አስታውቋል። የሳድክ የስብሰባ ጥሪ፤ በደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ ተልዕኮ ስር በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባል የነበሩ የደቡብ አፍሪካ እና የማላዊ ወታደሮች በጎማ መገደላቸውን ተከትሎ የመጣ ነው። በሩዋንዳ ይደገፋል የሚባለው ኤም23 አማጺ ቡድን በምስራቅ ኮንጎ ከፍተኛ ግስጋሴ እያደረገ እንደሆነ እየተነገረ ይገኛል። ሩዋንዳ ለኤም23 ቡድን ወታደራዊ ድጋፍ እንደማትሰጥ ብትገልፅም፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሩዋንዳ በምስራቅ ኮንጎ 4,000 ወታደሮች እንዳሰማራች እና ቡድኑን "በቀጥታ" እንደምታዝ መረጃ አለኝ ይላል። ሩዋንዳ በበኩሏ ከ1994ቱ የሩዋንዳ ዘር ማጥፋት ጋር ግኑኝነት አለው የምትለው የሩዋንዳ ነፃ አውጪ ዲሞክራሲያዊ ኃይል በኮንጎ ይደገፋል ስትል ትከሳለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0