የኢትዮጵያ ትልቅ ገበያ የሩሲያ ድርጅቶች ፍላጎት እየሳበ ነው አምባሳደር ኢቭጌኒ ቴርኪሂን ከኢዝቬስቲአ ጋር በብቸኝነት በነበራቸው ቆይታ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪሂን የኢትዮጵያ ትልቅ ገበያ የሩሲያን ድርጅቶች ቀልብ እየሳበ ነው ብለዋል። በዚህም ምክንያት የሩሲያ ድርጅቶች ወደፊት ከፍተኛ ተስፋ ባላቸው ፕሮጀክቶች በተለይም በአውቶሞቲቭ፣ በኤሌትሪካል ኢንጂነሪንግ እና በኬሚካል ኢንዱስትሪዎች ለመሳተፍ እያሰቡ እንደሆነ ገልጸዋል። አምባሳደሩ ጨምረውም በሁለቱ ሀገራት መሀከል ያለው ግንኙነት በሁሉም ዘርፎች እያደገ ነው ብለዋል። በሀገራቱ መሀከል ያለውን የአየር ትራንስፖርት የማስፋፋት እድልንም አምባሳደሩ በቃለ መጥይቃቸው ወቅት ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያን የብሪክስ አባልነት አስመልክቶ፤ የሩሲያ ሚና ከፍተኛ መሆኑን እና አዲስ የሆነ የአፍሪካ እይታም በብሪክስ ህብረት ውስጥ አስፈላጊ መሆኑን አምባሳደር ቴሬክሂን አስረድተዋል።አምባሳደሩ፤ ከአፍሪካ አምስተኛው ትልቅ ኢኮኖሚ የሆነችው ኢትዮጵያ ባለፈው የበጀት አመት ያስመዘገበችውን 8.1 በመቶ የጂዲፒ እድገት በጣም አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል። ጨምረውም 120 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ ለሩሲያ ምርት እና አገልግሎቶች ከፍተኛ ተስፋ ያለው ገበያ አላት ብለዋል።በድሬዳዋ ነፃ የገበያ ዞን ውስጥ እና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት በሩሲያ በኩል መኖሩን አምባሰደሩ አስረድተዋል። የሩሲያ ድርጅቶች በተለይም በመኪና ምርት፣ በኬሚካል፣ በኤሌትሪክ፣ በምግብ ኢንዱስትሪዎች እና በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ፕሮጀክቶች ላይ ለመሳተፍ እንደሚፈልጉ ጠቅሰዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያ ትልቅ ገበያ የሩሲያ ድርጅቶች ፍላጎት እየሳበ ነው አምባሳደር ኢቭጌኒ ቴርኪሂን
የኢትዮጵያ ትልቅ ገበያ የሩሲያ ድርጅቶች ፍላጎት እየሳበ ነው አምባሳደር ኢቭጌኒ ቴርኪሂን
Sputnik አፍሪካ
የኢትዩጵያ ትልቅ ገበያ የሩሲያ ድርጅቶች ፍላጎት እየሳበ ነው አምባሳደር ኢቭጌኝ ቴርኪሂን ከኢዝቬስቲአ ጋር በብቸኝነት በነበራቸው ቆይታ አምባሳደር ኤቭጌኝ ቴርኪሂን እንዳሉት የኢትዮጵያ ትልቅ ገበያ የሩሲያን ድርጅቶች ቀልብ እየሳበ ነው፤ በዚህም... 01.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-01T20:22+0300
2025-02-01T20:22+0300
2025-02-01T21:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የኢትዮጵያ ትልቅ ገበያ የሩሲያ ድርጅቶች ፍላጎት እየሳበ ነው አምባሳደር ኢቭጌኒ ቴርኪሂን
20:22 01.02.2025 (የተሻሻለ: 21:44 01.02.2025)
ሰብስክራይብ