በሩሲያው ዩናይትድ ፓርቲ እና በብልፅግና ፓርቲ መሀከል ያለው በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ትብብር  በግዜ ሂደት ውስጥ እየተስፋፋ የሚሄድ ነው በማለት የሩሲያው ባለስልጣን ተናገሩ

ሰብስክራይብ
በሩሲያው ዩናይትድ ፓርቲ እና በብልፅግና ፓርቲ መሀከል ያለው በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ትብብር  በግዜ ሂደት ውስጥ እየተስፋፋ የሚሄድ ነው በማለት የሩሲያው ባለስልጣን ተናገሩ የሩሲያ የደህንነት ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ እና የሩሲያ ዩናይትድ ፓርቲ መሪ ድሚትሪ ሜድቬዴ ለብልፅግና ጉባኤ ተሳታፊዎች ሰላምታቸው ልከዋል። በሁለቱ ፓርቲዎች መሀከል ያለው ትብብር በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረክ እንዲሁም በብሪክስ እና በሩሲያ-አፍሪካ የትብብር ፎረም እያደገ እንደሚመጣ ጠቁመዋል።ባለስልጣኑ አፅንኦት በመስጠት እንደተናገሩት የሩሲያ ዩናይትድ ፓርቲ በተለይም ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ያለውን ግንኙነት አስበልጦ እንዲጠናከር እና ግንኙነታቸው እንዲያድግ ውይይታቸውን በሀገራት ነፃነት ማእቀፍ ውስጥ እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል። ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቆየ ጠንካራ የሆነ ወዳጅነት አላቸው ያሉት ሜድቬዴቭ፤ ይህ ግንኙነት አሁን ለሚያደርጉት የፖለቲካ ውይይት እንደ መነሻ የሚያገለግል እንዲሁም የንግድ እና የሰብዓዊነት ግንኙነታቸውን የሚያጠናክር ነው ሲሉ አክለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0