የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፓትሩሼቭ የሩሲያ-አልጄሪያ በይነመንግስታት ኮሚሽን ስብሰባን መሩ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፓትሩሼቭ የሩሲያ-አልጄሪያ በይነመንግስታት ኮሚሽን ስብሰባን መሩየሩሲያው ዲሚትሪ ፓትሩሼቭ ከአልጄሪያ የግብርና፣ የገጠር ልማትና የዓሣ ማጥመድ ሚኒስትር ዩሱፍ ቸርፍ በጋር ሊቀመንበርነት ተካትፈዋል።ሁለቱ አካላት በሀገራቱ መካከል በኢነርጂ፣ በኢንዱስትሪ፣ በግብርና፣ በትራንስፖርት እና በመድኃኒት መስኮች በሚደረገው ትብብር ላይ ተወያይተዋል። እንደ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ ፤ ሩሲያ የሃላል ምርቶችን አቅርቦት ለማሳደግ እየሰራች ሲሆን የሩሲያ የእንስሳት ክትባቶች አቅርቦት ውጤታማ የስራ ዘርፍ ሊሆን ይችላል።‍ የአልጄሪያ ዜጎችም በሩሲያ ዩኒቨርስቲዎች የመማር ፍላጎት እያደገ ነው። በዚህ የትምህርት ዓመት ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ የአልጄሪያ ተማሪዎች በሩሲያ ውስጥ እየተማሩ ሲሆን ለእነሱ ያለው ኮታም ያለማቋረጥ እየጨመረ ነው።‍ በሩሲያ እና በአልጄሪያ ዲፓርትመንቶች መካከል የተቋቋመው በይነ መንግስታዊ ኮሚሽን ስብሰባን ተከትሎ በትምህርት እና በሳይንስ ፣ በኢኮኖሚ እና ስታንዳርዳይዜሽን መስክ በርካታ የሁለትዮሽ ሰነዶች መፈረማቸውን የሩሲያ መንግስት አስታውቋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0