የመንግስት የንግድ ድርጅት የሆነው ኢትዩ-ኢንጂነሪንግ በሀገር ውስጥ የኤሌትሪክ መኪኖችን ለማምረት ማቀዱን አስታወቀ

ሰብስክራይብ
የመንግስት የንግድ ድርጅት የሆነው ኢትዩ-ኢንጂነሪንግ በሀገር ውስጥ የኤሌትሪክ መኪኖችን ለማምረት ማቀዱን አስታወቀ የቡድኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሱሌማን ደደፎ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪን ለማምረት የሚገለግለው ሊትየም የተባለው ማእድን በስፋት ይገኛል። በዝቅተኛ ዋጋ ወደ ውጭ የሚላከውን ሂደቱ ያላላቀ ሊቲየም በሀገር ውስጥ በማስቀረት እና የመኪናውን ባትሪ እዚሁ ለማምረት የሚያስችል ቴክኖሎጂን ከሚያቀርቡ አካላት ጋር ትብብር በማድረግ ላይ መሆናቸውን ስራ አስፈፃሚው ጨምረው ተናግረዋል። ቡድኑ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን የማምረት አቅም ያላቸው 550 ከፍተኛ ብቃት ያላቸው ኢንጂነሮች  እንዳሉት ሱሌማን ጨምረው ተናግረዋል። ኢትዩ- ኢንጅነሪንግ ቡድን በሚኒስትሮች ምክርቤት ደንብ ቁጥር 475/2013 በመስከረም 2013  እንደ አዲስ የተቋቋመ የመንግስት የንግድ ድርጅት ነው።ይህ ቡድን እንደገና መቋቋም ያስፈለገው  በሀገሪቱ ያለውን ከባድ ኢንዱስትሪ እንዲመራ፤ ሀገሪቷ ራሷን ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመቀየር የወጠነችውን አላማ ማሳካት እንድትችል የመሪነቱን ስፍራ እንዲወስድ ነው በማለት ስራ አስፈፃሚው ለሚዲያዎች ተናግረዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0