በቻድ የሚገኙ ሶስት የፈረንሳይ የጦር ሰፈሮች ሙሉ በሙሉ ለቻድ ጦር ተላለፉ

ሰብስክራይብ
በቻድ የሚገኙ ሶስት የፈረንሳይ የጦር ሰፈሮች ሙሉ በሙሉ ለቻድ ጦር ተላለፉ እንደ የቻድ ጦር ኃይሎች ገለፃ፤ የፈረንሳይ ጦር በዋና ከተማዋ እንጃሚና የሚገኘውንና የመጨረሻውን ሰርጀንት አጂ ኮሲ የጦር ሰፈር በትላንትናው እለት ለአፍሪካዊቷ ሀገር አስረክቧል። የጦር ሰፈሩ ርክክብ የፈረንሳይ ጦር ከቻድ መሬት ሙሉ ለሙሉ መውጣቱን የሚያረጋግጥ ነው ሲል የቻድ ጦር ኃይል አመልክቷል። የቻድ ብሔራዊ ጦር የተመለሱትን የጦር ሰፈሮች ለማስተዳደር ዝግጁ እንደሆነ የቻድ ባለሥልጣናት መናገራቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0