300 ሚሊዮን አፍሪካውያንን በ2030 የኤሌትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ የተነሳው ሚሽን 300 የ50 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱን የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታወቀበመጪዎቹ አምስት አመታት 300 ሚሊዮን አፍሪካውያንን የኤሌትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ ሚሽን 300 በሚል መሪ ቃል በታንዛኒያዋ ዳሬሰላም እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ የኃይል ጉባኤ ከአለም ባንክ፣ ከአፍሪካ የልማት ባንክ እና ከኢስላሚክ የልማት ባንክ፣ ከኢሲያ የመሰረተ ልማት እና ኢንቨስትመንት ባንክ፣ ከፈረንሳይ የልማት ኤጄንሲ እና ከኦፔክ ፈንድ አጋሮች በትንሹ 53.95 ቢሊዩን ዶላር የፕሮጀክት ማስፈፀሚያ ማግኘቱን የአፍሪካ ልማት ባንክ መግለጫ አስነብቧል። "እቅዳችንን በአፍሪካ ከሚገኙት 600 ሚሊዮን ኤሌክትሪክ ኃይል ከማያገኙ ዜጎች ለግማሹ የኤሌትሪክ ኃይል ማቅረብ ነው። ይህንን እቅዳችንን ለማሳካት ብቻችን ማድረግ እንደማንችል የታወቀ እውነት ነው። በመንግስታት፣ በንግድ ተቋማት፣ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና በልማት ባንኮች ትብብር ብቻ ነው ይሄንን ማድረግ የምንችለው " ሲሉ የአለም ባንክ ፕሬዝዳንት አጃዬ ባንጋ በጉባኤው የጎንዩሽ ኩነት ላይ ተናግረዋል።30 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ባሳለፈነው ሰኞ እና ማክሰኞ እለት በተደረገው ጉባኤ ላይ ተመጣጣኝ እና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2030 እንዲስፋፋ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳውቀዋል። በጉባኤው ኃይልን ተደራሽ ለማድረግ ሀገራቱ አስፈላጊ የሆነ ለውጦች ላይ በመስራት 600 ሚሊዮን ሰዎችን ኤሌትሪክ አልባ ያደረገውን ችግር ለመታገል ቆርጠው እንደሚነሱ ቃል ገብተዋል ሲል የባንኩ መግለጫ ተነቧል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
300 ሚሊዮን አፍሪካውያንን በ2030 የኤሌትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ የተነሳው ሚሽን 300 የ50 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱን የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታወቀ
300 ሚሊዮን አፍሪካውያንን በ2030 የኤሌትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ የተነሳው ሚሽን 300 የ50 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱን የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታወቀ
Sputnik አፍሪካ
በጎርጎሮሳውያኑ 2030 ፤ 300 ሚሊዩን አፍሪካውያንን የኤሌትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ የተነሳው ሚሽን 300 የ50 ቢሊዩን ዶላር የገንዘብ እገዛ ማግኘቱን የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታወቀበመጪዎቹ አምስት አመታት 300 ሚሊዩን አፍሪካውያንን የኤሌትሪክ... 30.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-30T14:18+0300
2025-01-30T14:18+0300
2025-01-30T16:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
300 ሚሊዮን አፍሪካውያንን በ2030 የኤሌትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ የተነሳው ሚሽን 300 የ50 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱን የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታወቀ
14:18 30.01.2025 (የተሻሻለ: 16:14 30.01.2025)
ሰብስክራይብ