የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴህራን ከአለምአቀፉ የኒኩሌር ኤጀንሲ ጋር ትብብሯን ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላት አረጋገጡ

ሰብስክራይብ
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴህራን ከአለምአቀፉ የኒኩሌር ኤጀንሲ ጋር ትብብሯን ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላት አረጋገጡ " የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የሆኑት ፤ ሰይድ አባስ አራግህቺ እና የአለምአቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ  ኤጀንሲ ሀላፊ ራፋኤል ግሮሲ በኢራን እና በኤጀንሲው መሀከል ያለውን ትብብር  እና በቴክኒካዊ ጉዳዩች ላይ ያለቸውን ግንኙነት አስመልክቶ የስልክ ልውውጥ አድርገዋል።  አራግህቺ የኢራንን በድጋሚ  ከኤጀንሲው ጋር ለመተባበር ያላትን ዝግጁነት አስረድተዋል " በማለት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል።በተመሳሳይ ቀን የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አራግሃቺ ከብሪታንያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፀሀፊ ከሆኑት ዳቪድ  ላምይ ጋር ፦  የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ፣ የኑኩሌር ድርድሮች  እና የክልሉን ልማት አመልክቶ በስልክ ተወያይተዋል። " በዚህ በሀቅ በተደረገው ውይይት አራግህቺ የቴህራንን ኒኩለርን ለሰላማዊ የኃይል ምንጭነት  ለመጠቀም ላይ ያለውን  አቋም አሳውቀዋል። አፅንኦት በመስጠትም ባላት መርህን እና የራሷን ፍላጎት ባስጠበቀ መልኩ  የእስላማዊው ሪፐብሊኳ ኢራን ሁልግዜም ቢሆን ለድርድር ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል። ጨምሮም ይሄ አቋም አዲስ ያለመሆኑን እና ከዚህ በፊት በነበሩ ድርድሮች ላይ ኢራን ስትጠቀምባቸው ነበሩ እንደሆኑ አስታውሰዋል" በማለት የሚኒስትሩ መግለጫ አክሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0