በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ኮንግረንስ ላይ ለመሳተፍ ከእህት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወከሉ መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ነው

ሰብስክራይብ
በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ኮንግረንስ ላይ ለመሳተፍ ከእህት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወከሉ መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ነውከገቡት የፓርቲ መሪዎች  እና ተወካዩች መሀከል የቀድሞ የግብርና  ሚኒስትር እና የሞሮኮ ናሽናል ራሊ ፎር ኢንዲፔንደንስ ፓርቲ ተወካይ ሞሃመድ ሳዲቅ ፣ ዌላርስ ጋሳማጌራ የሩዋንዳ ፓትሮቲክ ፍሮንት ዋና ፀሀፊ ፣ ዛፈር ሲራካያ የቱርክ የጀስቲስ ኤንድ ዲቬሎፕመንት ፓርቲ ምክትል ሰብሳቢ እና የአልጄሪያ ናሽናል ሊብሬሽን ፍሮንት ዋና ፀሀፊ አብደልክሪም ቤንምባሬክ ይገኙበታል።እንግዶቹ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት የሞቀ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በአቀባበሉ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ ኢድርስ ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምክትል ሚኒስትር ብርቱካን አያኖ ፣ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክና ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ፒኤችዲ) እና የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ፒኤችዲ) ተሳትፈዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፣ የዲሞክራሲ ስረአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማእከል ሀላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር የሆኑት አዳም ፋራህ እንደተናገሩት ፤ ይህ ኮንግረንስ የፓርቲውን ቁመና የሚያሳድግ እና የሀገሪቷን እድገት  የሚያስቀጥል ውሳኔዎች ያስተላልፋል ተብሎ ይገመታል። ከአፍሪካ ትልልቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው ብልፅግና ፓርቲ በኮንግረንሱ ፦ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶች  ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ከ15 የተለያዩ ሀገራት እህት የፖለቲካ ፓርቲዎች የተወጣጡ  በአጠቃላይ 1,700 በላይ ተሳታፊዎችን የሚያሳትፍ ነው በማለት ሚዲያዎች ዘግበዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0