የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቁራን እና የአዛን ውድድር መካሄድ ጀመረ

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቁራን እና የአዛን ውድድር መካሄድ ጀመረ ከተለያዩ ዓለም ክፍል የተወጣጡ እንግዶች ውድድሩ ላይ ለመካፈል አዲስ አበባ ገብተዋል። በዛሬው እለት የተጀመረው እና ለአምስት ቀን የሚቆየው ውድድር ለሁለተኛ ዙር በመካሄድ ላይ ይገኛል።ከ60 ሀገራት የመጡ ከ100 በላይ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል። የውድድሩ ተሳታፊዎች በሀገሪቱ የሚገኙ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎችን ይጎበኛሉም ተብሎ ይጠበቃል። ዓለም አቀፉ የቁርአንና አዛን ውድድር በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና በዘይድ ኢብን ሳቢት የቁርዓን ማኅበር በጋራ የተዘጋጀ ነው። የተለያዩ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ኮንፈረሶችን የማዘጋጀት አቅሟ እያደገ የመጣው ኢትዮጵያ በርካታ ኩነቶችን በማስተናገድ ላይ እንደምትገኝ የሀገር ውስጥ ሚዲያ በዘገባው ጠቁሟል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0