ሞስኮ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኤም23 የፈጸመውን ድርጊት ማውገዟን የሩሲያ መልዕክተኛ ገለጹ

ሰብስክራይብ
ሞስኮ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኤም23 የፈጸመውን ድርጊት ማውገዟን የሩሲያ መልዕክተኛ ገለጹ"ሩሲያ በኤም 23 ቡድን የተፈጸመውን ድርጊት አጥብቃ አውግዛለች። ግጭቱ በአፋጣኝ እንዲቆም እና የዚህ ህገወጥ የታጠቀ ቡድን ተዋጊዎች ከያዙት ግዛቶች እንዲወጡ ጥሪ እናቀርባለን። የውጭ ተዋናዮችም ለኤም 23 የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያቆሙ እና የታጠቁ ክፍሎቻቸውን እንዲያስወጡ ጥሪ እናቀርባለን" በማለት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩሲያ መልዕክተኛ ቫሲሊ ኔቤንዚያ በድርጅቱ የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።በኮንጎ ግዛት ሰሜን ኪቩ ያለው ሁኔታ ወደ "እውነተኛ የሰብአዊ አደጋ" እየተቀየረ ሲሆን ዋና ከተማዋ ጎማ ከቀሪው ዓለም ተለይታለች፤ ይህም ለከተማዋ ህዝብ እና ለተፈናቀሉ ሰዎች ከባድ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል ብለዋል።"በዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች ላይ የሚደርሰውን ማንኛውንም ጥቃት ወይም የጥቃት ማሳያ እናወግዛለን። እንዲህ ዓይነቶቹ ድርጊቶች ሰላማዊ ሰልፍ ከማድረግ ጋር የሚያመሳስላቸው ነገር የለም። በቬየና ስምምነት እና በዓለም አቀፍ ግዴታዎች መሠረት ለውጭ ተልዕኮዎች ጥበቃ እንዲያደርግ ለኪንሻሳ ጥሪ እናቀርባለን" ሲሉ ተናግረዋል።ምስራቃዊ ኮንጎ ከተማ ጎማ በኤም 23 እና በመንግስት ኃይሎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ደርሷል። በግጭቱ ወደ 1,000 የሚጠጉ ሰዎችም መቁሰላቸውን እና በርካታ አስከሬኖች በጎዳናዎች ላይ መታየታቸውን አንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ ዕለት ዘግቧል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0