ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በብሪክስ ማዕቀፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በብሪክስ ማዕቀፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኢኖንሴባ ሎሲን አነጋግረዋል። የቆየና ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ፤ ትብብራቸውን የበለጠ ማጠናከር በሚችሉባቸው መንገዶች ዙርያ መክረዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁለቱ ሀገራት አፍሪካ ኀብረትን ጨምሮ በበርካታ ባለብዙ መድረኮች ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል። የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ኢኖንሴባ ሎሲ በበኩላቸው ግንኙነቱን ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሠሩ ገልፀው፤ ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባሻገር በአፍሪከ ህብረት፣ በብሪክስ ማዕቀፍ እንዲሁም በሌሎች ዓለም ዓቀፍ መድረኮች የጋራ ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኙ ምሥሎች መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0