የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጎማ ከተማ በአማጺያን ቁጥጥር ስር እንደገባ ተሠማ

ሰብስክራይብ
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጎማ ከተማ በአማጺያን ቁጥጥር ስር እንደገባ ተሠማ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ኃይል ኃላፊ ቢንቱ ኬይታ ቀደም ብለው እንደተናገሩት፤ የኤም23 አማፂያን ቡድን እና የሩዋንዳ ጦር የኮንጎ ሪፐብሊክ ሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው የጎማ ከተማ ዳርቻዎች ገብተዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ሩዋንዳ ወታደሮቿን ከኮንጎ እንድታስወጣ ጥሪ አቅርበዋል። የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ስማቸው ያልተጠቀሰ የአማፂ ቡድኑ መሪ፤ የዲሞክራሲያዊ ኮንጎ መንግሥት ወታደሮች በ48 ሰዓት እጃቸውን እንዲሰጡ ያስቀመጡት የግዜ ገደብ ተገባዷል። እ.አ.አ ሐምሌ 2022 በምስራቅ ኮንጎ የኤም23 አማጺያን እንቅስቃሴ በጨመረበት ወቅት አንጎላ ውስጥ የመሪዎች ስብሰባ ተካሂዶ ነበር። ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሩዋንዳ አማፂያኑን ትደግፋለች ስትል የከሰሰች ሲሆን ሩዋንዳ ግን ክሱን አስተባብላለች። ሁለቱ ሀገራት በድንበር አካባቢዎች በሚፈፀም ጥቃት እርስ በእርሳቸው ተወቃቅሰዋል። በስብሰባው የኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ እና የሩዋንዳው አቻቸው ፖል ካጋሜ ውጥረቱን ለማርገብ ተስማምተዋል። በስብሰባው ላይ የቀረበው ፍኖተ ካርታ ተኩስ በአስቸኳይ እንዲቆም እና የኤሜ23 አማጺያን ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ለቀው እንዲወጡ ጠይቋል። ሆኖም የኤም23 አማፂያን ቡድን በዚህ ፍኖተ ካርታ እንደማይገዛ አስታውቀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0