የኢትዮጵያና ሶማሊያ ስምምነት ቀጣናዊ ግኑኝነትን ያጠናክራል ሲል ኢጋድ ገለጸ

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያና ሶማሊያ ስምምነት ቀጣናዊ ግኑኝነትን ያጠናክራል ሲል ኢጋድ ገለጸ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት በቅርቡ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተደረሰው ስምምነት የምስራቅ አፍሪካን ቀጣናዊ ትብብር ለማጠናከር ወሳኝ ነው ሲል አወድሶታል። የአንካራውን ስምምነት ለዚህ የትብብር መጠናከር በማጣቀሻነት ያነሱት የኢጋድ የሰላምና ደኅንነት ክፍል ኃላፊ አበበ ሙሉነህ፤ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ አመራሮች ከስምምነቱ በኋላ ያደረጓቸው ጉብኝቶች የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል። ስምምነቱ በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነት ላይ በጎ ተጽዕኖ የማሳደር አቅም እንዳለውም ከሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ገልጸዋል። ስምምነቱ በዋነኛነት በሰላማዊ ውይይት አማካኝነት የተሻለ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ የትብብር መንገድ እንደሚከፍት ኃላፊው አስረድተዋል። ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ ወደ ነበረበት መመለሱ እና እየተካሄዱ ያሉ ውይይቶች በሁለቱ ሀገራት መካከል ከዚህ በፊት የነበሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ትልቅ አስተዋፅዖ እንዳላቸውም ጨምረው ገልፀዋል። ባለስልጣኑ አክለውም የቀጣናው ሀገራት ለውስጥ ጉዳዮቻቸው ቅድሚያ እንዲሰጡ እና የውጭ ጣልቃገብነትን ውድቅ እንዲያደርጉ ጥሪ በማቅረብ፤ ይህ አካሄድ ለክልላዊ አንድነት አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0