ጋናዊቷ ዲፕሎማት በሊቢያ የተመድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ተሾሙ

ሰብስክራይብ
ጋናዊቷ ዲፕሎማት በሊቢያ የተመድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ተሾሙ ሃና ሰርዋ ቴቴህ የዋና ጸሃፊው ልዩ ተወካይ እና በሊቢያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተልዕኮ ኃላፊ ሆነው እንደተሾሙ ተመድ በመግለጫው አስታውቋል። የቀድሞው የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሊቢያው ግጭት እ.አ.አ በ2011 ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ኃላፊነቱን የያዙ አሥረኛው ሰው ይሆናሉ። "ወ/ሮ ቴቴህ ከ2022 እስከ 2024 የአፍሪካ ቀንድ ዋና ፀሀፊ ልዩ መልዕክተኛ በመሆን ያገለገሉትን ጨምሮ በሀገር አቀፍ፣ በክልላዊ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የአስርተ ዓመታት ልምድን አካብተዋል" ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል። ቴቴህ ከ2018 እስከ 2020 በአፍሪካ ህብረት የዋና ፀሀፊው ልዩ ተወካይ የነበሩ ሲሆን፤ ናይሮቢ በሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነውም አገልግለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0