ኡጋንዳ በጎርጎርሳውያኑ 2023 ፀረ-ግብሰዶማውያን ህጎችን ካፀደቀች በኋላ አሜሪካ ያቋረጠችውን የንግድ ተጠቃሚነት መመለስ እንደምትፈልግ ገለጸች

ሰብስክራይብ
ኡጋንዳ በጎርጎርሳውያኑ 2023 ፀረ-ግብሰዶማውያን ህጎችን ካፀደቀች በኋላ አሜሪካ ያቋረጠችውን የንግድ ተጠቃሚነት መመለስ እንደምትፈልግ ገለጸች "በተቻለ ፍጥነት ከአዲሱ አስተዳደር ጋር ንግግር እንጀምራለን" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ቋሚ ፀሐፊ ቪንሰንት ዋይስዋ ባጊሬ ገልጸዋል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸውን ጠቅሰዋል።ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራት ያለ ቀረጥ ምርቶችን  ወደ አሜሪካ እንዲልኩ የሚፈቅደው ከነጻ የንግድ ስምምነት (አጎዋ) ጊዜው በመጪው መስከረም ላይ ያበቃል። ዋነኛው የቡና ላኪ የሆነችው ኡጋንዳ በፀረ-ግብረ ሶዶማውያን* ህጎች ምክንያት ከዚህ ፕሮግራም ተገላለች። ይህም በአምስት ዓመታት ውስጥ እስከ 8.3 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን የዓለም ባንክ ብድር እዳይለቀቅላት ምክንያት ሆኗል ሲል  የዓለም አቀፉ ኩባንያዎች ጥምረት ኦፕን ፎር ቢዝነስ ባደረገው ጥናት አመልክቷል።ትራምፕ በዚህ ሳምንት በመጀመሪያ የስልጣን ቀናቸው  ግብረ ሶዶማውያን ጥበቃዎችን ወደ ኋላ የሚመልሱ እና የመንግስት ብዝሃነት ፕሮግራሞችን የሚያቋርጡ ትዕዛዞችን ፈርመዋል።* “የግብረ ሶዶማውያን እንቅስቃሴ" በሩሲያ ባለሥልጣናት እንደ ጽንፈኝነት የሚቆጥር እና የታገደ ተግባር ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0