የጋና የካናቢስ ኢንዱስትሪ ለአገሪቱ በጀት 1 ቢሊዮን ዶላር ሊያመጣ እንደሚችል ሪፖርት ገለጸ"ከአንድ ሄክታር ካናቢስ ብቻ ቢያንስ 10,000 ዶላር ማግኘት ይቻላል። ይህ 50 ቢሊዮን ዶላር ኢንዱስትሪ ነው። ጋና በዓመት ቢያንስ 1 ቢሊዮን ዶላር ከካናቢስ ማግኘት ከቻለች የጋና ኢኮኖሚን ዳግም ያስነሳል" ሲሉ የካናቢስ ኢንዱስትሪ ቻምበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዳርኮ መናገራቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ይህንን ያሉት አርሶ አደሮች ካናቢስን እንዴት እንደሚያሳድጉ እና እንደሚሰሩ ለማስተማር በማለም በአክራ በተቋቋመው የካናቢስ ቻምበር የሥልጠና ማዕከል ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ነው ።የቻምበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መንግስት የሰብል በዛህነትን ለማሻሻል እና ገቢን ለማሳደግ በካናቢስ ዘርፍ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርግ አሳስበዋል፤ የጋና የአየር ንብረት ተስማሚ መሆኑንም ገልጸዋል።ዳርኮ፤ የኢንዱስትሪያል ካናቢስ ልማትን የሚፈቅደውን የናርኮቲክስ ቁጥጥር ኮሚሽን አዲስ ረቂቅ ህግን በመጥቀስ የካናቢስ ህክምና ምርት አቅም መኖሩን እና በአሜሪካ እና አውሮፓ የታቀደ ከፍተኛ ገቢ መታየታቸውን አፅንዖት ሰጥተዋል። በአለም አቀፍ የህክምና ገበያ የካናቢስ ገቢ በጎርጎሮሳውያኑ 2025 21.04 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ መገመቱን ገለልተኛ የምርምር ድርጅት ስታቲስቲክ ያመላክታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የጋና የካናቢስ ኢንዱስትሪ ለአገሪቱ በጀት 1 ቢሊዮን ዶላር ሊያመጣ እንደሚችል ሪፖርት ገለጸ
የጋና የካናቢስ ኢንዱስትሪ ለአገሪቱ በጀት 1 ቢሊዮን ዶላር ሊያመጣ እንደሚችል ሪፖርት ገለጸ
Sputnik አፍሪካ
የጋና የካናቢስ ኢንዱስትሪ ለአገሪቱ በጀት 1 ቢሊዮን ዶላር ሊያመጣ እንደሚችል ሪፖርት ገለጸ"ከአንድ ሄክታር ካናቢስ ብቻ ቢያንስ 10,000 ዶላር ማግኘት ይቻላል። ይህ 50 ቢሊዮን ዶላር ኢንዱስትሪ ነው። ጋና በዓመት ቢያንስ 1 ቢሊዮን ዶላር ከካናቢስ... 23.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-23T12:57+0300
2025-01-23T12:57+0300
2025-01-23T13:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የጋና የካናቢስ ኢንዱስትሪ ለአገሪቱ በጀት 1 ቢሊዮን ዶላር ሊያመጣ እንደሚችል ሪፖርት ገለጸ
12:57 23.01.2025 (የተሻሻለ: 13:14 23.01.2025)
ሰብስክራይብ