የአፍሪካ ኢኮኖሚ በጎርጎሮሳዊያኑ 2050 ፤ 29 ትሪሊዩን ዶላር ይደርሳል በማለት የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ኢኮኖሚ በጎርጎሮሳዊያኑ 2050 ፤ 29 ትሪሊዩን ዶላር ይደርሳል በማለት የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ተናገሩ   " በጎርጎሮሳዊያኑ 2050  የናይጄሪያ ህዝብ ቁጥር የአሜሪካንን የህዝብ ቁጥር ይበልጣል ፤ ይህም የአለም ሶስተኛ ትልቅ የህዝብ ቁጥር ያላት ሀገር የሚያደርጋት ይሆናል" በማለት ካሺም ሼቲማ አስረድተዋል።ሼትማ አፅንኦት ሰጥተው የአፍሪካ ነፃ የንግድ  ቀጠና የአፍሪካውያን የጋራ መዳረሻ እንዲሁም ከኢንዱስትሪያል የእውቀት ጊዜ በኋላ አፍሪካ ያላትን የመምራት አቅም ማሳደጊያ ነው ብለዋል ፤  ምንም እንኳን የግብርና እና የኢንዱስትሪ እድሎች ቢያልፏትም አሁንም እድል እንዳላት ተናግረዋል። ባለስልጣኑ አክሎም የአፍሪካ ፈጣን የዲጂታላይዜሽን እድገት እያስመዘገበች በማለት የ220 ሚሊዩን የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚዎችን እና 163 ሚሊዩን  በናይጄሪያ ብቻ የሚገኙ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በዋቢነት በመጠቀስ  " ይህም ህዝባችንን ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ እድል ፈጥሮናል" ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0