በአፍሪካ ሽብርተኝነት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ያስከተለው ስጋት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር  ገለጹ

ሰብስክራይብ
በአፍሪካ ሽብርተኝነት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩ ያስከተለው ስጋት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር  ገለጹ"በአፍሪካ እየጨመረ የመጣው ሽብርተኝነት ያስከተለው ስጋት እጅግ ከባድ እና አስደንጋጭ ነው። [...] አሳሳቢ ደረጃ  ላይ ደርሰናል እናም በጋራ እርምጃ መውሰድ አለብን"  ሲሉ የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ጸጥታ ኮሚሽነር ባንኮሌ አዶዬ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በአፍሪካ ሽብርተኝነትን መዋጋት ላይ ባካሄደው የሚንስትሮች ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።በጎርጎሮሳውያኑ 2024 ብቻ በአህጉሪቱ ከ3,400 በላይ ጥቃቶች መፈጸማቸውን እና 13,900 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል። ሽብርተኝነት ልማትን አደጋ ላይ የሚጥል፣ አስተዳደርን የሚያዳክም እና የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 2030 አጀንዳን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አዶዬ ጠቁመዋል። እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ የአፍሪካ ህብረት በአፍሪካ አመራርነት ላይ በማተኮር እና ጠንካራ አቅም በመገንባት በአዳዲስ ማዕቀፎች ምላሽ እየሰጠ ነው። ዋነኛ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የውስጥ እና የውጭ ቀጠናዊ የፀረ-ሽብርተኝነት ምላሽ ዘላቂነት እንዲረጋገጥ አዲስ አህጉራዊ ስትራቴጂካዊ የተግባር መርሃ ግብርን እንዲሁም የክልል ትብብርን እና የሽብርተኝነትን ፋይናንስ በአጠቃላይ ጥናት መፍታት ናቸው።"የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሽብርተኝነት ላይ ለመዋጋት በሚደረገው ትግል ሰላምን ለማስፈን የሚያስችለውን ተጠባቂ፣ ዘላቂና ተለዋዋጭ የገንዘብ ድጋፍን በጋራ መደገፍ አለባቸው" ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0