ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የተሰበሰበ ኃይል ፤ የሳህል አገራት ጥምረት የ5 ሺህ ሰዎች የጋራ ኃይልን አቋቋመየኒጀር የመከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ሳሊፉ ሞዲ ከኤክቱኒጀር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ይህ የጋራ ኃይል ለቀጠናዊ ትብብር፣ ለመቋቋም እና በራስ ችሎታ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የሳህል አገራት ጥምረት የጋራ ኃይል በአየር፣ መሬት እና በመረጃ አቅም በመላ አባል ሀገሮቹ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲሠራ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። ይህ ተነሳሽነት የተጀመረው በአፍሪካ የሽብርተኝነት ድርጊት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመጣበት ወቅት ነው ። የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፉት አስርት ዓመታት የሽብር ጥቃቶች በ400 በመቶ መጨመሩን ሪፖርት አድርጓል፤ በዚህም ሳሄል በአሁኑ ጊዜ ከዓለም አቀፍ ሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የሚከሰት ሞት ግማሽ ያህሉን ይይዛል ተብሏል። ጠንካራ አካባቢያዊ መፍትሄዎች አስፈላጊ መሆናቸውንም አፅንዖት ሰጥቷል።ከአቸኳይ ወታደራዊ ግቦቹ ባሻገር የጋራ ኃይሉ የሳሄል ቀጠና ለበለጠ ሉዓላዊነት እና ትብብር ያላቸውን ምኞቶችም ያካተተ ነው። ጄኔራል ሞዲ "ጦርነቱ የሁሉም ጦርነት ነው" በሚል አፅንዖት ሰጥተው የጋራ ሀብቶችን እና ቀጠናዊ መረጋጋትን ለማስፈን ፤ መንግስታትን፣ የአከባቢውን ህዝብ እና ዓለም አቀፍ አጋሮችን አንድ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የተሰበሰበ ኃይል ፤ የሳህል አገራት ጥምረት የ5 ሺህ ሰዎች የጋራ ኃይልን አቋቋመ
ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የተሰበሰበ ኃይል ፤ የሳህል አገራት ጥምረት የ5 ሺህ ሰዎች የጋራ ኃይልን አቋቋመ
Sputnik አፍሪካ
ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የተሰበሰበ ኃይል ፤ የሳህል አገራት ጥምረት የ5 ሺህ ሰዎች የጋራ ኃይልን አቋቋመየኒጀር የመከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ሳሊፉ ሞዲ ከኤክቱኒጀር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ ይህ የጋራ ኃይል ለቀጠናዊ ትብብር፣ ለመቋቋም እና በራስ... 22.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-22T19:35+0300
2025-01-22T19:35+0300
2025-01-22T20:24+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የተሰበሰበ ኃይል ፤ የሳህል አገራት ጥምረት የ5 ሺህ ሰዎች የጋራ ኃይልን አቋቋመ
19:35 22.01.2025 (የተሻሻለ: 20:24 22.01.2025)
ሰብስክራይብ