የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር "በጣም በቅርቡ" ለመነጋገር ማቀዳቸውን ገለጹ

ሰብስክራይብ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር "በጣም በቅርቡ" ለመነጋገር ማቀዳቸውን ገለጹ"በጣም በቅርቡ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር እንነጋገራለን" ሲሉ ትራምፕ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። አክለውም ባለፈው አርብ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ስለ ዩክሬን ቀውስ መነጋገራቸውን ገልጸዋል። የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የዩክሬኑ ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ግጭት የሰላም መፍትሄን ለማየት እንደሚፈልጉ ማሳወቃቸውን ገለጸው ፤ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በሰላም ስምምነት ለመደራደር ፈቃደኛ ካልሆነች አሜሪካ አዳዲስ ማዕቀቦችን ለመጣል ዝግጁ ናት ብለዋል። "ዜለንስኪ ሰላም እንዲሰፍን ይፈልጋሉ። ሰላም እንዲኖር እንደሚፈልግ በጥብቅ ነው የነገረኝ ነገር ግን የሁለቱም ፍቃድ ያስፈልጋል። ምን እንደሚከሰት እናያለን" ብለዋል ትራምፕ።የአሜሪካው መሪ እንዳሉት አስተዳደራቸው ለዩክሬን የጦር መሳሪያ አቅርቦት መቀጠል አለመቀጠል ጉዳይን እየመረመረ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0