ናይጄሪያ የዴትይ ዲሴመበር ፌስቲቫልን በመጠቀም የቱሪዝምን እድገቷን ለማሳካት እና ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ አቅዳለች

ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ የዴትይ ዲሴመበር ፌስቲቫልን በመጠቀም የቱሪዝምን እድገቷን ለማሳካት እና ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ አቅዳለችናይጀሪያ ለአንድ ወር ያህል በሙዚቃ ድግስ ፣ በፋሽን ትርኢት እና በምግብ ዝግጅቶች የሚቆየውን የዴትይ ዲሴሜበር ፌስቲቫልን ኢኮኖሚዋን ለማሳደጊያ እና የውጭ ምንዛሪን መሳቢያ መንገድ አድርጋ ለመጠቀም አቅዳለች።በሌጎስ ብቻ ይህ ፌስቲቫል 71.6 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የሚያስገኝ ሲሆን የ1.2 ሚሊዮን ጎብኚዎችን ቀልብ ይስባል ፤ ከላይ ከተጠቀሱት ጎብኚዎች 90 በመቶው በላይ የናይጄሪያ ዲያስፖራዎች መሆናቸውን የግዛቲቱን የቱሪዝም፣ ኪነ ጥበብ እና ባህል ልዩ አማካሪ ኢድሪስ አሬግቤ በመጥቀስ የሀገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል። ባለስልጣናት አሁን ላይ ይህንን ፌስቲቫል ማእከላዊ ለማድረግ እና ወደ ሌሎች ከተሞች ለማስፋፋት እየሰሩ ይገኛሉ ፤ ምክንያቱም ይህ ፌስቲቫል የባህል  ማሳያ እና ወሳኝ የቱሪዝም ማንቀሳቀሻ መድረክ እየሆነ በመምጣቱ ነው ተብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0