በዲሞክራሲያዊት የኮንጎ ሪፐብሊክ የሚገኙ የኤም 23 አማፂያን በሀገሪቱ ምስራቃዊ ግዛት በምትገኘው የሳኬ ከተማ ላይ በድጋሚ ጥቃት ፈፀሙበትላንትናው ምሽት አማፂያኑ ከሳኬ ከተማ ዙሪያ የሚገኝ የመንግስት ጦር ይዞታ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል በማለት የኮንጎ የዜና ማሰራጫ የሆነው አክቹሌት ዘግቧል። እስካሁን ድረስ የመንግስት ወታደሮች የአማፂያኑን ጥቃት መመከት ችለዋል። በመንግስት ጦር ቁጥጥር ስር ባለው የሳካ ተራራ ላይ ውጊያው የተጧጧፈ ሲሆን ከሞርታር በተተኮሰ ጥይት አማካኝነት እሳት ተነስቷል። በዉጊያዉ ስለደረሰው የመቁሰል አደጋ የተዘገበ ነገር የለም። በመንግሥት እና በአማፂያን መሀከል በሳኬ እየተደረገ ያለው ውጊያ የጀመረው በያዝነው የጥር ወር መጀመሪያ ነበር። ሳኬ የሰሜን ኪቩ ግዛት መቀመጫ ወደሆነችው የጎማ ከተማ መንገድ ላይ የምትገኝ እስትራቴጂካዊ ወሳኝ ከተማ ነቸ።ባለፈዉ የጎርጎሮሳውያኑ አመት አማፂያኑ በሩዋንዳ ድንበር አካባቢ የምትገኘውን የጎማ ከተማን ለመያዝ ወሳኝ የሆነችውን ሳኬን ለመያዝ ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም ነበር ።በሁለቱ ከተሞች መሀከል ያለው ርቀት 27 ኪሜ ብቻ ነው።አሁን ላይ ያለው ግጭት ቢቀጥልም ፤ በጎርጎሮሳዊያኑ ነሀሴ 2024 መንግስት እና አማፂው ኤም 23 በሰሜን ኪቩ የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራርመው ነበር።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በዲሞክራሲያዊት የኮንጎ ሪፐብሊክ የሚገኙ የኤም 23 አማፂያን በሀገሪቱ ምስራቃዊ ግዛት በምትገኘው የሳኬ ከተማ ላይ በድጋሚ ጥቃት ፈፀሙ
በዲሞክራሲያዊት የኮንጎ ሪፐብሊክ የሚገኙ የኤም 23 አማፂያን በሀገሪቱ ምስራቃዊ ግዛት በምትገኘው የሳኬ ከተማ ላይ በድጋሚ ጥቃት ፈፀሙ
Sputnik አፍሪካ
በዲሞክራሲያዊት የኮንጎ ሪፐብሊክ የሚገኙ የኤም 23 አማፂያን በሀገሪቱ ምስራቃዊ ግዛት በምትገኘው የሳኬ ከተማ ላይ በድጋሚ ጥቃት ፈፀሙበትላንትናው ምሽት አማፂያኑ ከሳኬ ከተማ ዙሪያ የሚገኝ የመንግስት ጦር ይዞታ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል በማለት የኮንጎ... 21.01.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-01-21T20:05+0300
2025-01-21T20:05+0300
2025-01-21T20:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በዲሞክራሲያዊት የኮንጎ ሪፐብሊክ የሚገኙ የኤም 23 አማፂያን በሀገሪቱ ምስራቃዊ ግዛት በምትገኘው የሳኬ ከተማ ላይ በድጋሚ ጥቃት ፈፀሙ
20:05 21.01.2025 (የተሻሻለ: 20:44 21.01.2025)
ሰብስክራይብ